የዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ ት/ት | Modern Accounting

Post

የዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ ት/ት | Modern Accounting

የሂሳብ አየያዝ፣ ሪፖርት ማድረግን እና የንግድ ሥራ አስተዳደርን ቀላል በሆነ መንገድ ለመረዳት በሚያስችሉ ተግባራዊ ትምህርቶች እናስተምራለን።

የሂሳብ እውቀትን ወደ ተግባራዊ የሥራ ክህሎት ይለውጡ፤ ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝን በተግባር ይማሩ።

የዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ ስልጠናችን የገንዘብ መዝገቦችን በትክክል ከመያዝ ጀምሮ የፋይናንስ ሪፖርቶችን ማዘጋጀት፣ የንግድ ሂሳብን መተንተን እና ዘመናዊ የሂሳብ ሶፍትዌሮችን በተግባር መጠቀም እንዲችሉ የተዘጋጀ ነው።

ስልጠናው ለጀማሪዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለሂሳብ ባለሙያዎች እና የሂሳብ እውቀታቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማሳደግ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ተስማሚ ነው።

የምንሰጣቸው ስልጠናዎች

  • Peachtree: የንግድ የሂሳብ መዝገቦችን ማደራጀት፣ ግብይቶችን መመዝገብ እና የፋይናንስ መረጃዎችን ማስተዳደር።
  • QuickBooks: የገቢና ወጪ መዝገብ፣ የንግድ ግብይቶችን መከታተል እና መሰረታዊ የፋይናንስ ሪፖርቶችን ማዘጋጀት።
  • SPSS: የመረጃ ማደራጀት፣ መሰረታዊ የመረጃ ትንተና እና የስታቲስቲክስ ውጤቶችን መረዳት።
  • STATA: የውሂብ ትንተና፣ የስታቲስቲካል ስራዎች እና የተለያዩ የመረጃ ስራዎችን በሶፍትዌሩ መፈጸም።
  • IFRS: ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ መርሆችን መረዳት እና በሂሳብ አያያዝ ላይ ተግባራዊ ማድረግ።

በስልጠናው ምን ያገኛሉ?

  • የገቢ፣ ወጪ እና የንግድ ግብይቶችን በትክክል የመመዝገብ ክህሎት
  • የፋይናንስ መረጃን በሶፍትዌር የማደራጀት እና የመተንተን ችሎታ
  • የተለያዩ የሂሳብ እና የፋይናንስ ሪፖርቶችን የመረዳት ችሎታ
  • ዘመናዊ የAccounting Software መሳሪያዎችን በተግባር የመጠቀም ክህሎት
  • የፋይናንስ መረጃን በመጠቀም ለንግድ ውሳኔ የሚረዱ መረጃዎችን የማዘጋጀት ችሎታ
  • የIFRS መሰረታዊ መርሆችን የመረዳት እና በስራ ላይ የመተግበር እውቀት

በተግባራዊ ትምህርት እና በተለያዩ የሂሳብ ሶፍትዌሮች ላይ በመለማመድ ተማሪዎች የሂሳብ መረጃን በትክክል እንዴት መመዝገብ፣ ማደራጀት፣ መተንተን እና ሪፖርት ማድረግ እንደሚችሉ ይማራሉ።

የሂሳብ እውቀትዎን ወደ ተግባራዊ የሥራ ክህሎት ይለውጡ፤ በዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ፣ በAccounting Software እና በፋይናንስ ሪፖርት ዝግጅት የተሻለ ክህሎት ይገንቡ።